የ 2020-2021 የዊንተር የአየር ሁኔታ

ለዊንተር አውሎ ነፋሶች የእኛ እቅድ

በ Seattle ውስጥ፣ ዊንተሩ በጣም ከባድ ዝናብ፣ ከፍተኛ ነፋሶች፣ በረዶ፣ እና ጥጥ የመሰለ በረዶ ሊያመጣ ይችላል። የዊንተር ማዕበሎች በሚመጡበት ጊዜ ደህንነትዎ የተጠበቀ መሆኑን እርግጠኛ ለማድረግ የ Seattle ትራንስፖርት ዲፓርትመንት (Seattle Department of Transportation) SDOT ሁኔታዎችን ይቆጣጠራል። ሰራተኞቻችን በቀጥታ መስመር ከ ብሄራዊ የአየር ንብረት አገልግሎት (National Weather Service) ጋር እና በቀጥታ ስርጭት ከ Doppler ራዳር ምላሽ ጋር አመቱን በሙሉ ለ 24 ሰአታቶች የአየር ሁኔታ ዘገባዎችን ይከተላሉ። }ማዕበል የተለያዩ አካባቢዎች ላይ ተጽዕኖ እንዴት እንደሚፈጥር ለማወቅ SNOWWATCHተብሎ የሚጠራውን }በዋሺንግተን (University of Washington) የተሰራውን የመተንበያ መሳሪያ እንጠቀማለን። ይህ መረጃ ቡድናችን መጀመሪያ የት እንደሚፈለጉ ለመወሰን ይረዳል። በከተማ ድልድዮች ላይ የሚገኙት የመሬት ቃኚዎች እና የኮምፒውተር ቃኚዎች ወቅታዊ እና ትክክለኛ የአየር እና የመኪና መንገድ ላይ የሙቀት መጠንን ይሰጣሉ። በዋና ጎዳናዎች ላይ በአሁኑ ጊዜ ያሉ ሁኔታዎችን ለማየት፣ በእውነተኛ ጊዜ፣ በቀጥታ-የሚያስተላልፉ ካሜራዎችን እንጠቀማለን። የካሜራው እይታዎችን በድህረ ገጻችን ላይ ማየት ይችላሉ፣ www.seattle.gov/travelers.

ግባችን Seattle እንቅስቃሴዋን ደህንነቷ በተጠበቀ እንድትቀጥል ነው

በከፋ የአውሎ ነፋስ ጊዜ፣ ቡድናችን የከተማውን ቁልፍ ጎዳናዎችን ለአውቶብሶች እና ለድንገተኛ ጊዜ አገልግሎቶች ነጻ ለማድረግ 24/7 ይሰራሉ። በረዶው መጣል ከመጀመሩ በፊት፣ በረዶው እንዳይጋገር ለመከላለከል ቡድናችን ቁልፍ ጎዳናዎችን እና ድልድዮችን በጸረ-በረዶ ማጥፊያ ቅድመ-መከላከል ያደርጋሉ። አንዴ በረዶ መጣል ከጀመረ በኋላ፣ ቡድናችን በተከታታይ መንገዶቻቸውን ማጽዳት እና በረዶ መጣሉን ሲቀጥል የሚያስፈልግበት ቦታ ላይ መንገዱን በጨው ማከም ይቀጥላሉ። ወደ 1200 የሚደርሱየሌን-ማይሎች ዋና ጎዳናዎች በ Seattle ውስጥ አሉ። ይሄን ሁሉ መሬት ለማፅዳት አውሎ ነፋሱ ከቆመ በኋላ እስከ 12 ሰዓታት ሊወስድ ይችላል። ዓለም አቀፍ አቀማመጥ ስርዓት (Global Positioning System) GPS የማረሻዎችን እና የጭነት መኪናዎች ያሉበትን ቦታዎች ይከታተላል። አንድ ጎዳና ምን ያህል በቀረበ ጊዜ እንደተጸዳ በድህረ ገጻችን ላይ ያለው ካርታ ያሳያል፡ www.seattle.gov/StormResponseMap

አመቱን በሙሉ ለበረዶ እንዘጋጃለን

በሰመር ውስጥ፣ ሰራተኞችን እናሠለጥናለን፣ መሣሪያዎችን እናስተካክላለን፣ እናም ከአከባቢው የወኪል አጋሮች ጋር እንሰራለን። ይሄ ማለት ከፍተኛ ነፋሶች፣ ከባድ ዝናብ፣ ወይም ጥጥ የመሰለ በረዶ እና በረዶ ሲተነበዩ ሰራተኞቻችን ወደ ሥራ ለመግባት ዝግጁ ናቸው ማለት ነው። የእነሱ ስራ መንገዶችን ከሁሉም ነገር ከወደቁ ዛፎች እና ቅርንጫፎች እስከ ጥጥ የመሰለ በረዶ እስከ በረዶን አጽድቶ ነጻ ማድረግ፣ እና ምልክቶችን እና አመላካቾችን መጠገን ነው። እንዲሁም የጨው እና የፈሳሽ ጸረ-በረዶ አቅራቦታችንን እንደተካመቹም እናረጋግጣለን።

የምዕራብ Seattle ከፍተኛ ከፍታ ድልድይ እና የኮቪድ -19 ምላሽ

ከክረምቱ ወራት ባሻገር በ ምዕራብ Seattle እና በ Duwamish Valley ውስጥ እና ዙሪያዋ ያሉ ተጓዦች በ 2020 በከፍተኛ ሁኔታ ተለውጠዋል። በሚቀጥሉት የተወሰኑ አመታት ውስጥ፣ ከዛ እና ወደዚያ ክልል የሚጓዙ ሰዎች በጨመረው መጨናነቅ የሚደርስባቸው ተጽዕኖ ይቀጥላል። በሁሉም ወቅታዊ በረዶ እና ነጫጭ በረዶዎች ባሉባቸው መንገዶች ምዕራብ Seattle ድልድይ ላይ የቅያሪ መንገዶች ማዘጋጀታችንን አረጋግጠናል። በዚህ ፈታኝ ጊዜ ሰዎች እና ሸቀጣሸቀጦች እንዲንቀሳቀሱ እንዴት መርዳት እንደሚችሉ ከዚህ በታች ተዘርዝራል፡

  1. በተቀያሪ መንገዶች ላይ የበለጠ የትራፊክ መጨናነቅ እንደሚኖር ያቅዱ እና ይጠብቁ።
  2. መድረሻዎ ላይ ለመድረስ ለእርስዎ ተጨማሪ ጊዜ ይስጡ።
  3. እንደ መራመድ፣ ሳይክል መንዳት፣ ወይም አውቶቡስ መጠቀም አይነት ያሉ አዲስ የመጓጓዣ መንገዶችን ይሞክሩ። የሚቻል ከሆነ፣ ለብቻዎ ከማሽከርከር ይቆጠቡ።
  4. ሊጠቀሙ በሚችሉባቸው ጎዳናዎች ላይ ለሚኖሩ ነዎሪዎች አሳቢ ይሁኑ እና አብሮዎት ለሚጓዙ ተጓዦች ቅንነት እና ትዕግስት ይኑርዎት።

በተጨማሪም ሁሉም የ COVID-19 የምርመራ ቦታዎች በ ዊንተር የአየር ሁኔታ ዕቅድ ውስጥ መሆናቸውን አረጋግጠናል። እና፣ ተጨማሪ ብዙ ጣቢያዎች ሲጨመሩ እና ቦታዎች ከተቀየሩ፣ እኛ ተለዋዋጭ ነን ስለዚህ በዛ መሰረት ልናስተካክል እንችላለን!

የእግረኛ መንገዶች የጸዱ እንደሆኑ እንዲቆዩ ለማድረግ የራስዎን ድርሻ ይወጡ

በዚህ ውስጥ ሁላችንም አብረን ነን እና በበረዶ አውሎነፋስ ወቅት በቤትዎ እና በንግድዎ ፊት ለፊት ያሉትን የእግረኛ መንገዶች እንደጸዱ እንዲቆዩ የማድረግ ሁሉም ሃላፊነት አለበት። በ Seattle ውስጥ ከ 2,400 ማይል የሚበልጡ የእግረኛ መንገዶች አሉ፣ እና የSDOT ሠራተኞች በአንድ ጊዜ ሁሉም ቦታ ላይ መሆን አይችሉም። የግለሰብ ሕንፃዎች አቅራቢያ ያልሆኑ የእግረኛ መንገዶችን በማፅዳት እና የከተማዋን ወሳኝ ቁልፍ ጎዳናዎች እንደጸዱ እንዲቆዩ በማድረግ ላይ ማተኮር እንድንችል እርስዎ ድርሻዎን እንደሚወጡ እርስዎ ላይ እንደገፋለን። በበረዶ ማዕበል ወቅት ሁሉም ሰው በተለይ አይነስውራን፣ አካልጉዳተኞች፣ ወይም ለመጓዝ የሚቸግራቸው ሰዎች በደህና መጓዝ እንዲችሉ ከቤትዎ ወይም ከንግድዎ ፊትለፊት ያለውን የእግረኛ መንገድን ማጽዳት ህግ ብቻ አይደለም፣ ትክክለኛ ነገርም ነው። በማህበረሰብዎ ውስጥ እገዛ ማን እንደሚያስፈልገው ለማወቅ ከማዕበሉ በፊት ጎረቤቶችዎን ያነጋግሩ። እያንዳንዱ ሰው በደህንነት መጓዝ እንዲችል በአካባቢዎ ያሉት ሁሉም የእግረኛ መንገዶች ንጹ ሆነው እንዲቆዩ ለማድረግ ዕቅድ ለማውጣት፣ እና አንዱ አንዱን እንዲያግዝ በአንድነት ይስሩ።

እንዴት እንደሚዘጋጅ:

  • አውሎ ነፋሱ ከመምጣቱ በፊት ያከማቹ። የበረዶ አካፋ፣ አንድ ከረጢት የጎዳና ጨው ፣ የሚሞቁ ልብሶች፣ ተጨማሪ ብርድ ልብሶች፣ የእጅ ባትሪዎች፣ የመጀመሪያ ዕርዳታ መሣሪያዎች፣ እና ለሁሉም ቤተሰብ የሚሆን የሶስት ቀን ምግብ፣ ውሃ፣ እና መድኃኒት ያስፈልግዎታል።
  • በረዶው ከመስራቱ በፊት፣ በረዶ እንዳይጋገር ለመከላከል የድንጋይ ጨው (ወይም ለአካባቢ ተስማሚ የሆነ ሌላ ምርት) በስሱ ይርጩ።
  • አንዴ በረዶ መጣል ከጀመረ በኋላ፣ ነጫጩ በረዶ ወደ ግግር በረዶ ከመቀየሩ በፊት የእርስዎን የእግረኛ መንገድ በአካፋ በየ 12 ሰዓቱ ያጽዱት። የሚችሉ ከሆነ፣ ጥሩ ጎረቤት በመሆን በአካባቢዎ ማንኛውንም የጎርፍ ማስወገጃዎችን እና የማዕዘን መታጠፊያ መወጣጫዎችን እንዲጸዳ ያግዙ ወይም እገዛ ለሚያስፈልጋቸው ማናቸውም ጎረቤቶች የእርዳታ እጅዎን በመስጠት ይርዱ።

የክረምት የአየር ሁኔታ ወረቀታችንን ያውርዱ!